Tuesday, October 20, 2015

የጊዜ ጉዳይ
የጊዜ ከፍታ
የጊዜዉ ዝምታ
ጊዜ ስጡኝ ላንድ አፍታ
በአእምሮ በአሳብ ዝምታ
ስበላ ስጣጣ  ስለብስም ዝምታ
የሕይወት ጉዞ ከታምታታ
የኑሮ እንቆቅልሽ እስክፈታ፡፡
የአለቆች ብዛት  ጉዞ ሳይገታ
የእንቆቅልሽ ብዛት ሳፈታ
የቋጠሮ  ቁልፍ ምነዉ ጠፋ?
ይሁን እንጅ ይመጣል ከፍታ
ለጊዜዉ ዝምታ….
መከራ አይሆንም ጮርሶ ጌታ
ያበቃል የሰዉ ልጅ ዋይታ
የህይወት ዉል ቁልፍ መቀነቱ
አስረጅ ከጠፋ በሠዓቱ
የእንቆቅልሽ ዉል መብዛቱ
በዚያዉ አይቀርም ይነጋጋል ለሊቱ፡፡
አዎ የጊዜ ብዛት ዝምታ
የህይወት መጽሐፍ ብዛቱ
ገጽ ገለጻ ጊዜ ማጥፋቱ
ስክኖ ለጠበቀ አይቀርም ጊዜ መምጣቱ
የብቼኝነት ጣጣ ፍራቻ
የእንቆቅልሽ ብዛት ዛቻ
የህይወት ግጥም አጣን መምቻ
…ግን ይሁን የጊዜ  ባሮች
የነጻት አየር ናፋቆዎች
ጥንት ሲንፈጠር ነጸ ሰዎች
ዛሬ ግን የጊዜ ጉዳይ ሆኖ ባሮች፡፡
የጊዜ ከፍታ
የጊዜዉ ጉዳ ዝምታ…….

ኢያሱ ለገሠ

No comments:

Post a Comment