የዓረብ ዓለም ንግስት
በሕይወት ሳለች የሐዘን ልብስ ለብሳ
የመከራ እሳት በላይዋ አንግሳ ፣፣
ተጨንቃ ተጠባ ለቤተሰብ አባሳ
የጽናት ተምሳለት የቤተሰብ መሰሶ
ጠራ ግድግዳ …..የሕይወት ዉሎ
አልደረቀም የእንባ
ለመከራ እንጃራ ሲትል ባባ
አረብ መቺ ጅሮ አለዉ ልስማ
በአረብ ምድር ሲትል ቀና ደፍ
የኒ ማኛ ብሎ አንገት ልያስደፍ
የዓብ ዓለም ንገስት መቼ ልትሰማ
ጥድፍያ ተያይዘዋል ለማምለጥ ከጨለማ
የዓረብ ንግስቶች ቀንደርሶ ይኖራሉ በክብር ማማ
ነጻ ይወጣሉ በግፍ ከጨለማ፤፤
የሕወይት ዘመን እንጀራ ሲታሰፋ
ከመቼዉ አበዶ ይሆን የስድብ ጥሩባ የሚነፋ?
የዓረብ ዓለም ልእልት የቤተሰብ የመኖር ተስፋ
ሐዘኑዋን አትናገር በግፍ ምድር ብትከፍ፡፡
ያንተ ምላስ ምነዉ ከረፋ…….
የሀገር ሀግት ናቸዉ የዉበት እንቁ
ገረድ አለመሆንዋን ሕዝብ እወቁ
ሀገር ገዳይ መረዝ ምላሱ
ትውልድ ሲራገም በምድር የለም ወይ ንጉሱ?
ሠርቶ መኖር ከመሰለዉ ወርደት
ሀገር እና ሕዝብ ከመረገመ ይባለዉ አቶን እሳት፡፡
ካልወደዱ በዓረብ ምድር አይደፈር ሕልቁ
ስፈልጉ አረብ በሳጃ የምሞሽልቁ
ለእንጀራ ሲሉ የተገፉ ነጻነታቸዉን የሚወዱ
አትኩይ ባይነት ልብስ ልብሶ ሥራቸዉን የሚሠሩ
ጊዙዉ ሆኖ ማንንም የማይፈሩ የተወዲሮስ ልጆች ናቸዉ፡፡
ለአሠር መልስ እሰጠች ካልወወክ አሁኑኑ አሳፈረኝ ባዮች
የሞራል የመንፈስ ጅግኖች አንተ ግን ስም ሰጠሃቸዉ…
ጥቁር መጋረጃ ልብሶዉ ሠራተኞ ናቸዉ፡፡
ሲቀናቸዉ ማዳሜን በጡጫ የሚያትወለዉሉ እኛ ምስክር ነን
አልሞት ባይ ተጋዳይ
ዝምታን የመወያዉ ለገዳይ›….
አለቅላቅነት ካባ አዉልቆ ጥቃትን የማይወዱ
ለአንድ ደቅቃ ለዓረብ የማይሰግዱ
የጀግና ትውልድ ምሳለ… ቅኝ ግዛት አላቅም ባይዮች
የዓረብ ዓለም ሴት የእግር እሳት ናቸዉ ለአስመሳዮች፡፡
በል ተፋርድ.. የሀገር ሴት ጥለህ በቆሸሻ
ትሳደባለህ እንደ ስትሻ …
ከወደዱህ እስከ ሞት ይገዙልሃል ዘር ቀለም ሳይመርጡ
ከጠለሁ ደግሞ ይጨምሩብሃል እሳት ረመጡ
የዓረብ ዓለም ሴት የሀገር ጅግና ናት በእግር አትርገጡ ፡፡
ክቡር ናት እና አትድፈሩ ክብVን
የመከራን እሳት ረግጣ ልጅ ታስተማረች ቀና ሳትል ጎንበስ ብላ፡፡
Dr EYASU LEGESSE
No comments:
Post a Comment